“መዝሙሩማ” መዝሙር ነው – የኅብረ-ዜማ ውጤት፣ ሕዝብን ያስተሳሰረ – የአንድነት ሰንሰለት፤ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ – ከደቡብ እስከ ሰሜን… ተዳርሶ በድንገት፣ በቅብብሎሽ ያስተጋባ – የነጻነት አዝማች ልደት! ደራሲውም ሕዝብ ነው – መሳሪያውም ባህላዊ፣ ዘረኞችን እሚያሸማቅቅ፣ ግፈኞችን እሚያርበደብድ… ኃያል ድምፅ ምትሃታዊ! “መዝሙሩማ” መዝሙር ነው – የብሩህ ዘመን ብስራት፣ በደም ቀለም የተጻፈ! – እሚዘመር በሕዝብ አንደበት! […]
↧