አማኒ ኢብራሂም — “ያልታወቀው” የጥበብ ሰው!
“… ሰው እያለ አጠገባችን፣ ቅንነቱን ማየት ሲያመን ከኛው አብሮ በህይወት ቆሞ፣ መልካም ስሙን መጥራት ሲያንቀን፣ “ሰው ካልሞተ ወይ ካልሄደ አይነሳም” እንላለን። እንዲህ እያልን፣ ስንቱን ጠቢብ እየሸኘን፤ አበባውን ቀጥፈን ጥለን፣ አበባ እናስቀምጣለን!!” መቼም ያለ-ግጥም ፍቅር መኖር የሚሆንልኝ አይመስለኝም። ዛሬ...
View Articleአባቱን ነገረኝ
በአባቱ ወንበር ላይ ሳሎን ተቀምጦ በባዶ ግድግዳ ተግ ብሎ አፋጦ የፊቱን ሁኔታ እየለዋወጠ ትካዜ ተጭኖት ቃላት እያማጠ ዓይኑን አጨንቁሮ እየመረመረኝ እንደዚህ እያለ አባቱን ነገረኝ አባቴ… አባባ ኤጭ! አለ ፊቱን አጨማዶ ሁሉን ነገር ጠልቷል ውስጡ ሆኗል ባዶ በምሬት ኮምትሯል … በጥላቻ በግኗል … አስሬ ኤጭ! ይላል...
View Article“ሰው አይደለም ! …”አለኝ
ገና ቁጭ እንዳልኩኝ ቀጥሮኝ እንዳገኘኝ እከሌ ጨርሶ «ሰው አይደለም!» አለኝ ምነው? ምን አ’ረገህ ? «ሰው አይደለም!» ስልህ እኮ! ምን አ’ረገህ? «ሰው አይደለም!» አልኩህ። ቢራችንን አዘን በዝምታ ቆየን እንደገና ደግሞ ሳሉን እየሳለ አንገቱን ነቅንቆ «ሰው አይደለም!» አለ። ሰው ይመስላል አልኩኝ ስሜቱን ልረዳ...
View Articleአባተ መኩሪያ “ተንቀሳቃሹ ቴአትር ቤት” (1932 – 2008)
‹‹ጥበበኛ በጥበብ እግር ይመላለሳል›› (ጠቢብ የሐውር በእግር ጥበብ) እንዲሉ፣ አባተ መኩሪያ ከግማሽ ምታመት በዘለለ በኢትዮጵያ ቴአትር ሕዋ ውስጥ በጥበብ ለጥበብ ኖሯል፡፡ ለቴአትር እስትንፋሱ ነበርም ይሉታል፡፡ በርሱ ጥበብ ያለፉት ሁሉ፡፡ በጥበብ የባተው አዘጋጅ፣ የውዝዋዜ አሠልጣኝ (ኬሪዮግራፈር)፣ ጸሐፌ ተውኔት፣...
View Articleይድረስ ለእኛ—ከእኛ!
ይድረስ ለእኛ-ከእኛ! – ከላይ ልጀምር ካ’ናቱ፣ በብረት ኃይል ተከቦ – ከተኮፈሰው በከንቱ፣ ይድረስልኝማ ለወያኔ – ለጊዜያዊው ባለጉልበቱ፤ … “ለሕዝባዊነት መጣሁ” ብሎ – ሕዝብን በጥይት መቁላት የለምና፣ አቆልቁለህ እየውማ – የምትሄድበትን ጎዳና! የጭካኔ መጠንህ ጫፍ ደረሰ – የውሸት ቋትህ ሞላ፣ የ’እውቀት‘...
View Articleጀግና ውለጅ እባክሽ !
የምሁር መሃይም – ተባይ አላዋቂ፤ የመሃይም ኩፍስ – አስመሳይ አዋቂ፤ የጅብ ባለ ጊዜ – ታፋ መራጭ ከሽንጥ፤ ያንበሳ ልክስክስ – ልፋጭ የሚያላምጥ የቁራ ዕርግብ መሳይ – ሠላምን አብሳሪ፤ የፈረስ አዝጋሚ – የግመል ሰጋሪ፤ ንጹህ ሰው ታሳሪ – በፈጠራ ወንጀል፤ ፍርደ ገምድል ዳኛ – ፈራጅ በቂም በቀል፤ የባዕድ...
View Article“መዝሙሩማ…”!
“መዝሙሩማ” መዝሙር ነው – የኅብረ-ዜማ ውጤት፣ ሕዝብን ያስተሳሰረ – የአንድነት ሰንሰለት፤ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ – ከደቡብ እስከ ሰሜን… ተዳርሶ በድንገት፣ በቅብብሎሽ ያስተጋባ – የነጻነት አዝማች ልደት! ደራሲውም ሕዝብ ነው – መሳሪያውም ባህላዊ፣ ዘረኞችን እሚያሸማቅቅ፣ ግፈኞችን እሚያርበደብድ… ኃያል...
View Articleጉ፣ የአቶ ዠ ልጅ ወይም “ጉማሬው” ዋናተኛ
አቶ ዠ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ከተጫነባቸው በኋላ በUN ኢትዮጵያን ወክሎ የመቀመጥ ስልጣናቸው ቀረና ወደ ሌላ ሥልጣን ተሻገሩ። እድገት ወይም ውርደት (promotion ወይም demotion) ሳንል፣ ወደ ሌላ ሥልጣን ተሻገሩ እንላለን። አቶ ዠ የሃገሪቱ የዋና ፌዴሬሽን ፕሬዚደንት ሆነው ተሾሙ። እንግዲህ “ፕሬዚደንት”...
View Article“እንዳትረግጡት…. የኢትዮጵያን ዐፈር –መሬት!”
‘ባካችሁ ……… ’ባካችሁ………. እናንት በምድረ–ኢትዮጵያ ያላችሁ፤ “አትሂዱ …..በ‘ግራችሁ…” ከቻላችሁ ….. “ብረሩ ክንፍአው’ታችሁ።” ግን……..አደራ……….. ………. አንዳትረገጡት ……. መሬቱን እንዳታዩት……… አፈሩን፤ ብታርሱት…… አትዘሩበት ብዘሩበት …….. አይበቅልበት፤…….. ደምነውና – የትላንና– የዛሬ...
View Articleእናት ሀገር!
“አንቺ እማማ ኢትዮጵያ አንቺ እናት ዓለም” ሎሬትሽ እያቆላመጠ ይነግርሽ እንደነበር በቀለም፤ እወቂበት ከእንግዲህ አብጂለት ፍቱን መላ፣ የሚሞትልሽ እንጂ የሚገልሽ ላይበላ፤ ህዋሳትሽ ይንቀሳቀስ ሰሜን-ደቡብ ምዕራብ-ምስራቅ፣ የአለላ ተምሳሌቱ የሕዝቦችሽ ህብረት ይድመቅ፤ ብድግ በይ ተራመጂ በእንፉቅቅ መዳኽሽ...
View Articleይድረስ — ለኃይለማርያም ደሳለኝ!
ለ’ክቡር’ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ለኢሕአዴግ ሊቀ-መንበር፣ ጠቅላይ ‘አዛዥ’ ለ”አግዓዚ” ጦር…፤ ይድረስ ለአቶ ኃይለማርያም! በስምዎ ባዘሏት ወላዲተ-አምላክ.. በወልድ በእየሱስ ክርስቶስ ስም ልያዝዎ፣ ኢትዮጵያን በጥይት አያቃጥሏት… እግዚአብሔር አባት ይቅር ይበልዎ! በደርግም ሆነ በወያኔ ዘመን ባገር ያሴሩ፣ እስከዛሬ...
View Articleእኔ አማልሰጣችሁ፣ እናንተ እማትወስዱት! …
ያለ ስም፣ ስም – ስጡኝ ቅጡኝ፣ አስቀጡኝ፤ አግዙኝ፣ ወርውሩኝ፣ … በማጎሪያችሁ እሰሩት… እጀን፣ … በካቴናችሁ ‘ጠንዙት’ እግሬን፣ …. በእግር ብረታችሁ ቸንክሩት፣ ገንዙት፣ … ይደንዝዝላችሁ ሽባ ሆኘ ልቅር፣ ‘’ልሰንከልላችሁ’’:: ……… እንካችሁ …. ጀርባዬን መጫሚያ፣ መዳፌን፤ ግረፉት፣ አቃጥሉት፣ …. በኮረንቲ...
View Articleምነው! ፈጣሪ አምላክ!
አላለቅስም ያልኩት … እንባ የፈሪ ነው ብዬ ዋጥ ያ’ረኩት፣ አይቻል ተችሎኝ ይዤው የከረምኩት፣ ገንፍሎ ወጣና እንባዬ ፈሰሰ ጉንጮቼን ሰንጥቆ ፌቴን አዳረሰ በዛ እንባዬ መሀል አንገቴን አቅንቼ ለፈጣሪ ጮኽኩኝ! እጆቼን ዘርግቼ ምነው? ፈጣሪ አምላክ ምነው! ረሳኸን ምነው! ይሄን በደል አላይልን አልከን ምነው? የኛን...
View Articleየእናት ለቅሶ
እናት በፍቅር፣ ጽንስ ይዛ፣ ዘጠኝ ወር አርግዛ፣ ራስዋን ምግብ አድርጋ፣ በማኅጸንዋ ሸሽጋ፣ ሽሉን ወደሰውነት አሳድጋ፣ የፈጣሪን ባሕርይ ተጋርታ፣ ሰው ሆና ሰው ፈጣሪ የሕይወት አለኝታ፣ በጻዕር አምጣ ወልዳ፣ አቅፋ በፍቅር አጥብታ፣ ተጨንቃ አሳድጋ፣ እንቅልፍ አጥታ፣ ሲስቅ ሲያስቃት፣ ሲያለቅስ ሲያስለቅሳት፣ ስትቆጣው...
View Articleየፍቅር ብልሃቱ
ልዩነትን አድንቅ አንድነትን አድምቅ እንቆቅልሽ ፍታ ጥላቻ ይረታ ሁሉም ብሔረሰብ ነውና ቤተሰብ “እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ” ማለት ተውክ አማራ ምንም እንኳን በአገር መንፈስህ ቢኮራ “እኔ ኦሮሞ ነኝ” ማለት ተውክ ኦሮሞ ምንም እንኳን ጥሪህ ሁሎ ቢያድር ከርሞ “ኢትዮጵያዊ አማራ” ሆነህ ስትሄድ “ኢትዮጵያዊ ኦሮሞ” አገኘህ...
View Articleግፍና ጎርፍ
ሰሚ ካጡ የሶማሌ ተረቶች አንዱ እንዲህ ይላል፡፡ አንድ ሰው የጠፋች የአካባቢውን ግመል ፍለጋ ጫካ ይገባል፡፡ ከብዙ መከራ በኋላ ያቺን ግመል አግኝቶ ከተማ ገባና ግመሏን ለባለቤቱ ሳይመልስ ሐሳቡን ቀይሮ ራሱ ያልባትና ይጋልባት ጀመር፡፡ ግመሏን ከአውሬ ለማዳን ጫካ ገብቶ የነበረው ሰውዬ እርሱ ራሱ ግመሏን መውሰዱ...
View Articleእናቶች፣ “ሶሻል ሚዲያ”ና ህወሃት/ኢህአዴግ
አዲስ አበባ የሰፈር ሴቶችን ሰብስበው መግለጫ ስለ social media አጠቃቀም ስጡ ተብለው የሰጡት መግለጫ እና ከመግለጫው በኋላ ለእናቶች የተደረገ ኢንተርቪው። ዜና FBC ፦ “መንግስት በሶሻል ሚዲያው ላይ ህዝብ የሚቀሰቅሱትን ጸረ-ሰላም ሃይሎች ከሚኖሩበት አገር ጋር በመመካከር ለህግ ማቅረብ አለበት!” ሲሉ...
View Articleመሬቱ
ጥምል እየዞረ በሰማዩ ማገር በመሬቱ ዙሪያ ዕውነት የሚናገር ጠባሳው ያልጠፋ የታሪክ አሻራ መሬቱ መሰለኝ ጠላት የሚያፈራ። አገር በቀል ይሁን የሰው አገር ባዕዳ ዐይን እየማረከ የሚጋብዝ እንግዳ ከጥንት ጀምሮ እንደ እሚታወቀው ጠላት የሚያፈራ ለምለሙ መሬት ነው። ለምለሙ መሬት ነው ጦርነት አብቅሎ ቤት አልቦ ያስቀረኝ...
View Articleለመለስ የተፃፈ ደብዳቤና የመለስ መልስ
ከፍቃዱ ጌታቸው ለመለስ እንደምን አለህ ጋሼ እንደምን ነህ መለስ ትመጣለህ ስንል ቀረህ ሳትመለስ እኛማ ይሔውልህ ባንተ ሌጋሲና ባንተ ትልቅ ራዕይ በየአደባባዩ እንላለን ዋይ ዋይ ዛሬም ጀነራልህ ተኩስ ነው ትዕዛዙ ወገን ያጋድማል የግፍ አፈሙዙ ለምንድን ነው ስንል ስምክን አስቀድመው ከክርስቶስ በላይ ምስልህን አትመው...
View Articleላም እሳት ወለደች!
አጉል ዘመን ገጥሟት በረት ብትከሳ፤ ከብቶች በመዥገሮች አዩ ብዙ አበሳ፡፡ ጡቶቿን አቃጣይ የነበልባል ጥጃ ላም እሳት ወለደች፤ ብ’ተው በማይተዋ ዘልለው ባልጠገቡ ወይፈኖች ነደደች፡፡ የከበረው ባህል ባለጌ ረጋግጦት እንደጨው ቀለለ፤ ወፍ ዘራሾች ነግሠው ባጥለቀለቁት ደም ምድር ተበከለ፡፡ አዎ፣ ላም እሳት ወለደች!...
View Article