ትንሿ የ’ሕል ዘር፤ ዐይን እንኳ ብትገባ የማትቆረቁር፤ ድንገት ጠብ ብትል የማትገኝ ከምድር፤ ቁልቁል አሾልቃ በንቀት እያየች፤ በድሃው ወገኔ ከት ብላ ሳቀች! …….. እጅጉን አሾፈች:: አሹቅህን አውልቅ – ሽንብራህን ቆርጥም፤ ባቄላህን ጠርጥር – በቆሎህን ከርትም፤ እኔን ካሁን ወዲያ እንኳን ልትበላኝ፤ ድንገት በመንገድ ላይ ባይንህም አታየኝ፤ እያለች አፌዘች፤ በወገኔ ሳቀች !………. በወገኔ አሾፈች !! አረም እንዳይውጣት – […]
↧
ጤፍ እንኳን ባቅሟ!
↧
መልካም አዲስ ዓመት!
የታሪክ አምድ ነባራዊ፣ ምድረ-ህይወት ፍልስፍና፣ መውጣት መውረድ፣ የዓለም ህግ፣ የተፈጥሮ ገጽ ሆነና፣ ጊዜ ክፉ፣ ጊዜ ደጉ..፣ እጥፍ-ዘርጋ፣ ዘመም-ቀና..፣ አንዴ ጽልመት..፣ አንዴ ብርሃን..፣ ባለታሪክ፣ ባለዝና፤ ስትወድቂ..፣ ስትነሺ..፣ በዘመናት ጉዞሽ ሂደት፣ ለዚህ ደረስሽ፤ እልልልል! ሁለት ሺ ሰባት ዓመት! (ሙሉውን ግጥም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
↧
↧
“ኢትዮጵያ ቅደሚ!”
የቀድሞው የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር “ኢትዮጵያ ቅደሚ!” በይፋ (officially) ለህዝብ የተበሰረውና በ“አብዮት አደባባይ” የተዘመረው ልክ የዛሬ 40 አመት ቅዳሜ መስከረም 2 ቀን 1968 ዓ.ም ነበር! በርካታ የቀድሞ ተማሪዎቼና ወዳጆቼ በተገናኘን ቁጥር “የምንወደው መዝሙር ግጥም እየተዘነጋን ነውና እባክህ ባመቸህ መንገድ እንደገና አውጣው” እያሉ ሲጠይቁኝና እኔም ቃል ስገባ ብዙ ጊዜ ሆነን። 40ኛ አመቱን ምክንያት በማድረግ ለታሪክ ማስታወሻ እንዲሆን […]
↧
ሌቦ ነይ …
ማስታወሻ፤ ከጥቂት ሳምንታት በፊት አንድ የህወሃት አባል ወይም ተላላኪ እንደሆነ የታሰበ ግለሰብ 5 ሚሊዮን የእንግሊዝ ፓውንድ የሚገመት (በፎቶው እንደሚታየው) ጥሬ ገንዘብና ወርቅ በሻንጣው ይዞ ከኢትዮጵያ ወደ ለንደን እንግሊዝ ሲገባ ጋትዊክ አየር ማረፊያ ላይ በፖሊሶች ተይዟል። ግለሰቡ ለመጀመሪያ የፍርድ ምርመራ ፍርድ ቤት በቀረበ ጊዜ ዳኛው “ይህን ያክል ገንዘብ እንዴት በሻንጣ ልትይዝ ቻልክ?” የሚል ጥያቄ ሲያቀርቡ፣ ግለሰቡ […]
↧
እነኚህ ሰዎች ማናቸው? – ፲፱ መልስ
ከአዘጋጆቹ፤ ከጥቂት ወራት በፊት በወዳጃችን ወለላዬ ለቀረበው የበርካታ በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ አገዛዝ ዘመን የካቢኔ አባላት የነበሩ ባለሥልጣናትን ፎቶ ለያዘው ጥያቄ ምላሽ በመስጠት የተባበራችሁትን ሁሉ ከልብ እናመሰግናለን:: ከተለያዩ ምንጮ ያሰባሰቡትን ምላሽ ወለላዬ አጠር ካለች ግጥም ጋር በቁጥራቸው ቅደም ተከተል አቅርበውታል፡፡ ከዘመኑ መብዛትና መረጃ መዛባት ምክንያት በምላሹ ላይ ስማቸው ወይም ማዕረጋቸው የተዛባ ቢኖር ማስተካከያ ለሚሰጡ ሁሉ አሁንም በቅድሚያ […]
↧
↧
በንቁጣጣሽ! ምን ቀጠፈሽ?
ዘመን ፊትሽ ተከምሮ እየታዬ ስራሽ አምሮ እንቁጣጣሽ አንድ ብለሽ አርባ ድረስ እድሜ ቆጥረሽ እንደ ቤቶች የሳቅ ተውኔት እንደ ጨቤ ስካር ህይወት ሞት ራሱን ያሾፍሽበት ለምንድነው? በይ ንገሪኝ እባክሽን አደብቂኝ ባንቺው ቀዬ የተወለድኩ ፊደል በጄ እዛው የያዝኩ መስፍን ሜዳ የተራገጥኩ በጨበጣ ብይ ያስቆጠርኩ ቲቸር ታዬ ያስተማሩኝ ገብሬ ኩርኩም ያቀመሰኝ የሲሚንቶ ጭስ ያወዛኝ ቅዱስ ያሬድ ተሳልሜ ከሽፋ […]
↧
የተቆለፈበት ቁልፍ!
ከዶ/ር ምህረት ደበበ፣ የአዕምሮ ህክምና ስፔሺያሊስት፣ እ.አ በ2005 ዓ.ም የተጻፈ መጽሀፍ፣ 438 ገጽ ትችት! በዶ/ር ፈቃዱ በቀለ፣ የስልጣኔ ተመራማሪና የኢኮኖሚ ዕድገት ባለሙያ! ይህን መጽሀፍ አግኝቴ ለማንበብ እድል ያጋጠመኝ ከሁለት ሳምንት በፊት ባለቤቴ ወደ ኢትዮጵያ ሄዳ ስትመለስ ይዛልኝ ከመጣች በኋላ ነው። በዶ/ር ምህረት ደበበ የተጻፉ ሁለት ወፈፍራም መጽሀፎች ሲሆኑ፣ አንደኛው መጽሀፍና በቅርብ የወጣውን የሽፋኑ ሰዕል ደስ […]
↧
ዳሪና ቀባሪ
ዳሪ ወዳጄ እንደምነህ – ውዱ ጎረቤቴ ባለህበት ቦታ – ይድረስህ መልክቴ የልጄ ሰርግና – የሟች ልጅህ ቀብር አንድ ላይ መሆኑ – ፈጥሮብኛል ችግር መቼም ይገባሃል – ግልጽ ነው ነገሩ ብዙ ነው ማዕረጉ – የሠርገኛ ክብሩ ስለዚህ አደራ – የልጄን ታላቅ ሠርግ በደስታ በሆታ – እንዳሳልፍ በወግ በዛ ቀን ተነስተህ – ልጅህን ስትቀብር ስዎችን ሰብስበህ – […]
↧
“የናፈቀ ሰዉ በር በሩን የታከተ ሰዉ መስኮቱን ይመለከታል”በዕዉቀቱ ስዩም
ከዓመታት የንባብ ብህትዉና በኃላ በቀጣይ ሳምንት በመጽሃፍ መልኩ ብቅ የሚለዉ በዕዉቀቱ ስዩም፣ በርከት ያሉ ሞጋች ሃሳቦችን በሥነ-ጽሁፋዊ ለዛ እያዋዛ ወደ አደባባይ እንደሚያወጣ ጥርጥር የለዉም፡፡ “ከአሜን ባሻገር” ምን አለ? . . . የመራቂዉን ማንነት መፈተሸ …? ጥልቅ መጠይቅ …? ወይስ ለየት ያለ ፍንገጣ? … ብቻ ብዙ ነገር ይጠበቃል፡፡ በተለይ ጽዮን ተኮር ኃይማኖታዊ ባህልና መስመር ያለፈ ጥብቅ […]
↧
↧
አቶ ዠ፣ ጸሃፌ-ተውኔት
አቶ ዠ ከጸሃፌ-መፈክር ወደ ጸሃፌ-ተውኔት እሸጋግራለሁ ብለው መፈከራቸው እንዳለ ሆኖ፣ ይንን አስመልክቶም ለኢሃዴግ ፍቅር ቴአትር ቤት ሥራ አስቀማጭ ደብዳቤ መላካቸው እንዳለ ሆኖ፣ … ከወራት በኋላ የአቶ ዠ ባለቤት ወይዘሮ ዘ ቡና አፍልተው ከአቦል እስከ በረካ ተጠጥቶ እንዳለቀና ሥኒ እያጠቡ እያለ… ወይዘሮ ዘ ገረሙህ?“ባልና ሚስት ካንድ ባህር ይቀዳል” ሲባል አልሰማህም?ባላቸው ዠ ከሆኑ እሳቸው ከ ዘ ሌላ […]
↧
አንቺን አስታዋሼ
መቼ ትመጫለሽ መቼ ልጠብቅሽ ወይ መቼ ላምጣልሽ መቼ ላቀብልሽ ሽሮና . . . ምናምን ስለተላከልሽ ሽሮውን ውሰጂው በርበሬውን ውሰጅ ቅቤውንም ውሰጅ . . . ሚጥሚጣ ተይልኝ እሱ ስለሆነ – አንቺን ሚያስታውሰኝ ……………………….. ምን ይሰራልሀል ብቻውን ሚጥሚጣ ትደፋው የለም ወይ እንጀራ ስታጣ
↧
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፳
ከአዘጋጆቹ፤ በጎልጉል ወዳጅ ወለላዬ ጀማሪነትና አቀናባሪነት ሲስተናገድ የነበረው “እኚህ ሰው ማናቸው?” የተሰኘው ዝግጅታችን እንደገና ተጀምሯል፡፡ ለረጅም ጊዜ በመቋረጡ ይቅርታ እየጠየቅን አሁን ግን በወዳጃችን ወለላዬ ብርቱ ትጋት ለመጀመር በመቻላችን ለወለላዬ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ በዝግጅቱ ስትካፈሉ ለነበራችሁና መልሳችሁን ስትሰጡ ለነበራችሁ ሁሉ አሁንም ይህንኑ ማድረግ እንድትጀምሩ ልናሳስባችሁ እንወዳለን፡፡ የዝግጅቱ ዋና ዓላማ በአገራችን ስማቸውን ተክለው ያለፉ በፎቶ አስደግፎ የግጥም ጥያቄ […]
↧
የኢትዮጵያ የታሪክ ውዝግብ የወለደው አዲሱ የሕዝባዊ ታሪክ ፀሐፊና መርማሪ –በዕውቀቱ ሥዩም
እንደ – መግቢያ በኢትዮጵያ ታሪክ አፃፃፍ ላይ ብዙ ልዩነቶች ይስተዋላሉ፡፡ የልዩነቶቹ ሥረ-ምክንያት እንደ ጸሐፊው ማንነትና የሥርዓታቱን ባህሪ መነሻ ያደረገ ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ የኢትዮጵያን የቀደመ ታሪክ የሚቃኙ የተለያዩ ኃይለ-ሐሳቦች በየጊዜዉ እንዲጸባረቁ ግድ ብሏል፡፡ የታሪክ ትንቅንቁ በአጥቂነትና በተከላካይነት የሚበየን ነው፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ዙሪያ ፍልሰት፣ መስፋፋት፣ ብሔራዊ ጭቆና፣ ቅኝ ግዛትና መሰል ቃላት ላለፉት አርባ ዓመታት፤ በተለየ መልኩ ደግሞ […]
↧
↧
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፳፩
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ጊዜ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፳” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር ሃያ ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ መልስ በጌምድርና – ሰላሌን በመግዛት ጠቅላይ አዛዥ ሆነው – በጣሊያን ጦርነት በተንቤን ግንባር – ላይ ሌሎች የመሩ ልዑል […]
↧
ለንቅልፍህ አትሳሳ
የእንቅልፍ ምቀኛ (ከዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ) እወራረዳለሁ በአንድ ሚሊዮን ብር ሸለብ ሲያደርግህ ነው ስልክህ የሚል ቅርርር! ሚያዝያ 9፣ 2008 ዓ.ም. (አፕሪል 17፣ 2016 እ.ኤ.አ.)፤ ምንጭ፡- ፌስቡክ ምላሽ ለዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ለንቅልፍህ አትሳሳ ወለላዬ ይከሰታል አዎን! ልክ ነህ ዶክተሬ የት ይጠፋል ብለህ የሚል ፍቅሬ ፍቅሬ ደግሞም ትክክል ነው እንዳተ ለሚጽፍ በዚህ በአሁን ጊዜ ምን ይሠራል እንቅልፍ ላገራችን […]
↧
ማዕረግ እንስጣቸው!
ሰው በሕይወት ሳለ መቼም ማድነቅ አንወድ ማሻሻል አለብን ይሄን ነገር የግድ እኚህ ጠንካራ ሰው ፕሮፌሠር መስፍን ለራሳቸው ቢሆን የለፉት እስካሁን ሀብት ከሥልጣን ጋር በእጃቸው ጨብጠው በታዩ ነበረ ከሁሉ ሰው በልጠው ነገር ግን እኚህ ሰው ለሀገር ሲለፉ ምንም ሳይኖራቸው ዕድሜአቸውን ገፉ ሆኖም እንደሳቸው ከህሊናው አድሮ መኖር ክብር አለው እየበሉ ሽሮ ጥንትም ሆነ አሁን በተሳሳተ ሀገር መቼም […]
↧
እግርና ጫማ
እግርና ጫማ ተጣብቀው አንድ ላይ በክር ተሳስረው አብረው ውለው ስታይ እውነት አይምሰልህ ያ ሁሉ ፍቅራቸው ሲመሽ ወደማታ ሄደህ ብታያቸው በአንሶላ መካከል እግር ተዘርግቶ ጫማ በራፉ ላይ ወድቋል አፉን ከፍቶ!
↧
↧
ልዩ ጥበብ ገንባ
ፍቅር ታሞ ከርሞ አልጋ ላይ እንደሰው ብዙ ዘመን ሆነ ሞቶ ከቀበርነው ይሄ ሆኖ እያለ ሞቱን እያወቅን ለአያሌ ዓመታት ዘፋኞች በዘፈን አሁንም እንዳለ ህይወት እስትንፋሱ ጨርሶ እንዳልሞተ እንዳልወጣች ነፍሱ አድርገው ሲዘፍኑ ሲያቀብሉን ውሸት ነገሩን ዋጥ አድርገን አብረን ጨፈርንበት ከሁሉ ‘ሚገርመው የሚደንቀው ነገር አለ የሚባለው የአሁን ዘመን ፍቅር ገንዘብን ውሃልክ አ’ርጎ ተመስርቶ በዓይናችን እያየን መካካዱ ከፍቶ ዘፋኙ […]
↧
ስለቴክኖሎጂ ሊያነጋግር የከጀለ መጽሀፍ
የዛሬዋ ዓለማችን በደረሰችበት የእድገት ደረጃ ስልጣኔን ወይም ብልጽግናን ከቴክኖሎጂ ለይቶ ማየት ያስቸግራል። የሰለጠነ ህብረተሰብ ማለት ቴክኖሎጂን ያዳበረ ህብረተሰብ ማለት ነው። ባንጻሩም ቴክኖሎጂን ያላዳበረ ህብረተሰብ ማለት ደግሞ ያልበለጸገ ህብረተሰብ ነው። የሰለጠነ ህብረተሰብ ስንል ደግሞ ድኅነት የተረታበት፤ በሽታ የመነመንበት፤ ትምህርት የተስፋፋበት (እውቀት የለመለመበት)፤ ዲሞክራሲ የሰፈነበት፤ የመገናኛና ቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት በስፋት የተንሰራፋበትና ህግ የበላይ የሆነበት ህብረተሰብ ማለታችን ነው። ቴክኖሎጂ […]
↧
አስርቱ አምባገነናዊ ትዛዛት!
“እኔ ስላንተ በበረሐ ደሜን አፍስሻለሁና ከእኔና ከአጋሮቼ በቀር ሌላ የፖለቲካ ፖርቲ በቃልህ አትስበክ በልብህም አትመን”፤ “መንግስት የኛ ናትና ወደ መንግስት አትመልከት ስልጣኑንም አትመኝ”፤ “የባለስልጣናትን ጥፋት … የዜግነት መብቱንም በሶሻል ሚዲያ የተቸ እሱ ወዮለት፤ የባለስልጣን ሚስትም ቅምጥም ሃብትም የማይነኩ፤ የማይደፈሩ “ቅዱስ” ናቸውና ትንፍሽ እንዳትል!! ….” “ከደርግ ጨካኝ አገዛዝ አውጥቼሃለሁና… በፍፁም ልብህ በፍፁም ሃሳብህ ለእኔ ብቻ ተገዛ”፤ […]
↧