Quantcast
Channel: Goolgule
Viewing all 162 articles
Browse latest View live

አማኒ ኢብራሂም — “ያልታወቀው” የጥበብ ሰው!

$
0
0
“… ሰው እያለ አጠገባችን፣ ቅንነቱን ማየት ሲያመን ከኛው አብሮ በህይወት ቆሞ፣ መልካም ስሙን መጥራት ሲያንቀን፣ “ሰው ካልሞተ ወይ ካልሄደ አይነሳም” እንላለን። እንዲህ እያልን፣ ስንቱን ጠቢብ እየሸኘን፤ አበባውን ቀጥፈን ጥለን፣ አበባ እናስቀምጣለን!!” መቼም ያለ-ግጥም ፍቅር መኖር የሚሆንልኝ አይመስለኝም። ዛሬ ግን ብዕሬን ያነሳሁት ግጥም ለመጻፍ ባለመሆኑ፣ እነሆ ! የነብይ መኮንን የሆነችውን ይህቺን ግጥም፣ ለተነሳሁለት የጽሁፍ ጭብጥ እንደ […]

አባቱን ነገረኝ

$
0
0
በአባቱ ወንበር ላይ ሳሎን ተቀምጦ በባዶ ግድግዳ ተግ ብሎ አፋጦ የፊቱን ሁኔታ እየለዋወጠ ትካዜ ተጭኖት ቃላት እያማጠ ዓይኑን አጨንቁሮ እየመረመረኝ እንደዚህ እያለ አባቱን ነገረኝ አባቴ… አባባ ኤጭ! አለ ፊቱን አጨማዶ ሁሉን ነገር ጠልቷል ውስጡ ሆኗል ባዶ በምሬት ኮምትሯል … በጥላቻ በግኗል … አስሬ ኤጭ! ይላል አባባ ኤጭ! አለ እንደገና ደግሞ በሳሎኑ መሀል ተገትሮ ቆሞ እንደገና […]

“ሰው አይደለም ! …”አለኝ

$
0
0
ገና ቁጭ እንዳልኩኝ ቀጥሮኝ እንዳገኘኝ እከሌ ጨርሶ «ሰው አይደለም!»  አለኝ ምነው? ምን አ’ረገህ ? «ሰው አይደለም!» ስልህ እኮ! ምን አ’ረገህ? «ሰው አይደለም!» አልኩህ። ቢራችንን አዘን በዝምታ ቆየን እንደገና ደግሞ ሳሉን እየሳለ አንገቱን ነቅንቆ «ሰው አይደለም!» አለ። ሰው ይመስላል አልኩኝ ስሜቱን ልረዳ ፊቱን መረመርኩኝ ባ’ይኑ እየገረፈኝ አይምሰልህ! አለኝ ግንባሩ ታጠፈ ጥርሶቹን ነከሰ ጠረጴዛ መታ፣ ቢራችን ፈሰሰ […]

አባተ መኩሪያ “ተንቀሳቃሹ ቴአትር ቤት” (1932 – 2008)

$
0
0
‹‹ጥበበኛ በጥበብ እግር ይመላለሳል›› (ጠቢብ የሐውር በእግር ጥበብ) እንዲሉ፣ አባተ መኩሪያ ከግማሽ ምታመት በዘለለ በኢትዮጵያ ቴአትር ሕዋ ውስጥ በጥበብ ለጥበብ ኖሯል፡፡ ለቴአትር እስትንፋሱ ነበርም ይሉታል፡፡ በርሱ ጥበብ ያለፉት ሁሉ፡፡ በጥበብ የባተው አዘጋጅ፣ የውዝዋዜ አሠልጣኝ (ኬሪዮግራፈር)፣ ጸሐፌ ተውኔት፣ የፊልም አዘጋጅ የነበረው አባተ መኩሪያ በአገሪቱ የቴአትር ታሪክ ውስጥ ስማቸው በግዘፍ ከሚነሱትና አሻራቸውን ካሳረፉ በኩሮች አንዱ ነበር፡፡ በተለይ […]

ይድረስ ለእኛ—ከእኛ!

$
0
0
ይድረስ ለእኛ-ከእኛ! – ከላይ ልጀምር ካ’ናቱ፣ በብረት ኃይል ተከቦ – ከተኮፈሰው በከንቱ፣ ይድረስልኝማ ለወያኔ – ለጊዜያዊው ባለጉልበቱ፤ … “ለሕዝባዊነት መጣሁ” ብሎ – ሕዝብን በጥይት መቁላት የለምና፣ አቆልቁለህ እየውማ – የምትሄድበትን ጎዳና! የጭካኔ መጠንህ ጫፍ ደረሰ – የውሸት ቋትህ ሞላ፣ የ’እውቀት‘ ገደብህ አበቃ – ከእንግዲህ ላይኖርህ የቀረ ‘መላ’፣ ከወደቁ ወዲያ መንፈራገጥ.. እንዳይሆን ለመላላጥ፣ ሳሩንም ላለመጋጥ.. መሬቱንም […]

ጀግና ውለጅ እባክሽ !

$
0
0
የምሁር መሃይም – ተባይ አላዋቂ፤ የመሃይም ኩፍስ – አስመሳይ አዋቂ፤ የጅብ ባለ ጊዜ – ታፋ መራጭ ከሽንጥ፤ ያንበሳ ልክስክስ – ልፋጭ የሚያላምጥ የቁራ ዕርግብ መሳይ – ሠላምን አብሳሪ፤ የፈረስ አዝጋሚ – የግመል ሰጋሪ፤ ንጹህ ሰው ታሳሪ – በፈጠራ ወንጀል፤ ፍርደ ገምድል ዳኛ – ፈራጅ በቂም በቀል፤ የባዕድ ባለቤት – የነባር ባይተዋር፤ ሥልጡን ሥራ ፈቶ – […]

“መዝሙሩማ…”!

$
0
0
“መዝሙሩማ” መዝሙር ነው – የኅብረ-ዜማ ውጤት፣ ሕዝብን ያስተሳሰረ – የአንድነት ሰንሰለት፤ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ – ከደቡብ እስከ ሰሜን… ተዳርሶ በድንገት፣ በቅብብሎሽ ያስተጋባ – የነጻነት አዝማች ልደት! ደራሲውም ሕዝብ ነው – መሳሪያውም ባህላዊ፣ ዘረኞችን እሚያሸማቅቅ፣ ግፈኞችን እሚያርበደብድ…       ኃያል ድምፅ ምትሃታዊ! “መዝሙሩማ” መዝሙር ነው – የብሩህ ዘመን ብስራት፣ በደም ቀለም የተጻፈ! – እሚዘመር በሕዝብ አንደበት! […]

ጉ፣ የአቶ ዠ ልጅ ወይም “ጉማሬው” ዋናተኛ

$
0
0
አቶ ዠ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ከተጫነባቸው በኋላ በUN ኢትዮጵያን ወክሎ የመቀመጥ ስልጣናቸው ቀረና ወደ ሌላ ሥልጣን ተሻገሩ። እድገት ወይም ውርደት (promotion ወይም demotion) ሳንል፣ ወደ ሌላ ሥልጣን ተሻገሩ እንላለን። አቶ ዠ የሃገሪቱ የዋና ፌዴሬሽን ፕሬዚደንት ሆነው ተሾሙ። እንግዲህ “ፕሬዚደንት” የሚለው ቃል እስካለ ድረስ፣ ሹመቱ፣ ማዕረጉ ትልቅ ነው ተብሎ እንዲታሰብ የአቶ ዠ መልካም ፈቃድ ነው እንላለን። […]

“እንዳትረግጡት…. የኢትዮጵያን ዐፈር –መሬት!”

$
0
0
‘ባካችሁ ……… ’ባካችሁ………. እናንት በምድረ–ኢትዮጵያ ያላችሁ፤ “አትሂዱ …..በ‘ግራችሁ…” ከቻላችሁ ….. “ብረሩ ክንፍአው’ታችሁ።” ግን……..አደራ……….. ………. አንዳትረገጡት …….  መሬቱን እንዳታዩት………  አፈሩን፤ ብታርሱት…… አትዘሩበት ብዘሩበት …….. አይበቅልበት፤…….. ደምነውና – የትላንና– የዛሬ – የአሁን፣ ትኩስ…. የፈሰሰበት አጥንት ነውና ያልደረቀ፣ “አጸደ–ህይወት” የወደቀበት እናንተም ከእንግዲህ፣ ”ዐጽም – ‘ርስቴ” የማትሉት፤……….. ያውም ……………………………….. የባቶቻችሁ፣……..የናቶቻችሁ ያውም……………………………… የወንድሞቻችሁ፣……..የህቶቻችሁ ያውም…………………………………… የእቦቀቅላወቹ፣……የታዳጊወቹ፣……..የልጆቻችሁ፤ ዓይናችሁ እያየ፣…….እየሰማጆሮ‘ችሁ የተመቱ! …የቆሰሉ!….. የተወጉ! […]

እናት ሀገር!

$
0
0
“አንቺ እማማ ኢትዮጵያ  አንቺ እናት ዓለም” ሎሬትሽ እያቆላመጠ  ይነግርሽ እንደነበር በቀለም፤ እወቂበት ከእንግዲህ  አብጂለት ፍቱን መላ፣ የሚሞትልሽ እንጂ  የሚገልሽ ላይበላ፤ ህዋሳትሽ ይንቀሳቀስ  ሰሜን-ደቡብ ምዕራብ-ምስራቅ፣ የአለላ ተምሳሌቱ  የሕዝቦችሽ ህብረት ይድመቅ፤ ብድግ በይ ተራመጂ  በእንፉቅቅ መዳኽሽ ያብቃ፣ የውብ ህይወት አዲስ ምዕራፍ  በግዛትሽ ይገንባ! እናት አገር ባለታሪክ  ተነሽ ቤትሽን አጽጂ፣ የተዝረከረከውን   በፕሮፓጋንዳ ፈንጂ፣ በተከፈተው ጉድጓድ ይግባ  ጠራርገሽ አስወግጂ። […]

ይድረስ — ለኃይለማርያም ደሳለኝ!

$
0
0
ለ’ክቡር’ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ለኢሕአዴግ ሊቀ-መንበር፣ ጠቅላይ ‘አዛዥ’ ለ”አግዓዚ” ጦር…፤ ይድረስ ለአቶ ኃይለማርያም! በስምዎ ባዘሏት ወላዲተ-አምላክ.. በወልድ በእየሱስ ክርስቶስ ስም ልያዝዎ፣ ኢትዮጵያን በጥይት አያቃጥሏት… እግዚአብሔር አባት ይቅር ይበልዎ! በደርግም ሆነ በወያኔ ዘመን ባገር ያሴሩ፣ እስከዛሬ ሕዝብን ሲያስጨፈጭፉ የኖሩ፣ “እግዚአብሔርን አናውቅም” ብለው የካዱ ነበሩ፤ እርስዎ ግን፣ ከቤተሰብዎ ጋር ማዕድ ሲጋሩ፣ የየዕለቱን ጸሎትዎን ሲያበስሩ፣ የአምላክን ስም ነጋ-መሸ እየጠሩ፣ […]

እኔ አማልሰጣችሁ፣ እናንተ እማትወስዱት! …

$
0
0
ያለ ስም፣ ስም – ስጡኝ ቅጡኝ፣ አስቀጡኝ፤ አግዙኝ፣ ወርውሩኝ፣ … በማጎሪያችሁ እሰሩት… እጀን፣ … በካቴናችሁ ‘ጠንዙት’ እግሬን፣ …. በእግር ብረታችሁ ቸንክሩት፣ ገንዙት፣ … ይደንዝዝላችሁ ሽባ ሆኘ ልቅር፣ ‘’ልሰንከልላችሁ’’:: ……… እንካችሁ …. ጀርባዬን መጫሚያ፣ መዳፌን፤ ግረፉት፣ አቃጥሉት፣ …. በኮረንቲ ገመድ የሰራ አከላቴ፣ ይክሰል፣ ይሁን ዓመድ:: ……… ዝረፉት … ሀብቴን ቤትና ንብረቴን፣ በምድር ያለኝን፤ ሰብስቡ፣ አከማቹት፣ ለዓለም […]

ምነው! ፈጣሪ አምላክ!

$
0
0
አላለቅስም ያልኩት … እንባ የፈሪ ነው ብዬ ዋጥ ያ’ረኩት፣ አይቻል ተችሎኝ ይዤው የከረምኩት፣ ገንፍሎ ወጣና እንባዬ ፈሰሰ ጉንጮቼን ሰንጥቆ ፌቴን አዳረሰ በዛ እንባዬ መሀል አንገቴን አቅንቼ ለፈጣሪ ጮኽኩኝ! እጆቼን ዘርግቼ ምነው? ፈጣሪ አምላክ ምነው! ረሳኸን ምነው! ይሄን በደል አላይልን አልከን ምነው? የኛን ጩኸት ሰምተህ ጨከንክብን ብዬ ወተውትኩት አልኩበት እዬዬ አሁንም ይፈሳል አልቆመም እንባዬ ምነው! ፈጣሪ […]

የእናት ለቅሶ

$
0
0
እናት በፍቅር፣ ጽንስ ይዛ፣ ዘጠኝ ወር አርግዛ፣ ራስዋን ምግብ አድርጋ፣ በማኅጸንዋ ሸሽጋ፣ ሽሉን ወደሰውነት አሳድጋ፣ የፈጣሪን ባሕርይ ተጋርታ፣ ሰው ሆና ሰው ፈጣሪ የሕይወት አለኝታ፣ በጻዕር አምጣ ወልዳ፣ አቅፋ በፍቅር አጥብታ፣ ተጨንቃ አሳድጋ፣ እንቅልፍ አጥታ፣ ሲስቅ ሲያስቃት፣ ሲያለቅስ ሲያስለቅሳት፣ ስትቆጣው እንዲያድግላት እንዲማርላት፣ ክቡር ሰው ሆኖ እንዲያኮራት፣ ያላትን ሁሉ ከፍላ መስዋእት፣ በጉጉት ስትጠብቅ — ጨካኞች ሬሳውን ጣሉላት፡፡ […]

የፍቅር ብልሃቱ

$
0
0
ልዩነትን አድንቅ አንድነትን አድምቅ እንቆቅልሽ ፍታ ጥላቻ ይረታ ሁሉም ብሔረሰብ ነውና ቤተሰብ “እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ” ማለት ተውክ አማራ ምንም እንኳን በአገር መንፈስህ ቢኮራ “እኔ ኦሮሞ ነኝ” ማለት ተውክ ኦሮሞ ምንም እንኳን ጥሪህ  ሁሎ ቢያድር ከርሞ “ኢትዮጵያዊ አማራ” ሆነህ ስትሄድ “ኢትዮጵያዊ ኦሮሞ” አገኘህ መንገድ የልብ ትርታ ሲወጣ ገሃድ ብለው ሲጠብቁ እሳትና ጭድ ፍቅር ጣልቃ ገብቶ አደረገ […]

ግፍና ጎርፍ

$
0
0
ሰሚ ካጡ የሶማሌ ተረቶች አንዱ እንዲህ ይላል፡፡ አንድ ሰው የጠፋች የአካባቢውን ግመል ፍለጋ ጫካ ይገባል፡፡ ከብዙ መከራ በኋላ ያቺን ግመል አግኝቶ ከተማ ገባና ግመሏን ለባለቤቱ ሳይመልስ ሐሳቡን ቀይሮ ራሱ ያልባትና ይጋልባት ጀመር፡፡ ግመሏን ከአውሬ ለማዳን ጫካ ገብቶ የነበረው ሰውዬ እርሱ ራሱ ግመሏን መውሰዱ ብዙዎችን አስገረማቸው፡፡ ትንሽ ቆየና ከዚያች ከአንዷ ግመል ወተት እያለበ በግመሏ ላይ ተቀምጦ […]

እናቶች፣ “ሶሻል ሚዲያ”ና ህወሃት/ኢህአዴግ

$
0
0
አዲስ አበባ የሰፈር ሴቶችን ሰብስበው መግለጫ ስለ social media አጠቃቀም ስጡ ተብለው የሰጡት መግለጫ እና ከመግለጫው በኋላ ለእናቶች የተደረገ ኢንተርቪው። ዜና FBC ፦ “መንግስት በሶሻል ሚዲያው ላይ ህዝብ የሚቀሰቅሱትን ጸረ-ሰላም ሃይሎች ከሚኖሩበት አገር ጋር በመመካከር ለህግ ማቅረብ አለበት!” ሲሉ ነዋሪነታቸው በቀበሌ 07 ልደታ ክከ የሆነ እናቶች ተናገሩ … ↩ ከዜናው በኋላ የእናቶች ኢንተርቪው፦ ☞ የመጀመሪያዋ […]

መሬቱ

$
0
0
ጥምል እየዞረ በሰማዩ ማገር በመሬቱ ዙሪያ ዕውነት የሚናገር ጠባሳው ያልጠፋ የታሪክ አሻራ መሬቱ መሰለኝ ጠላት የሚያፈራ። አገር በቀል ይሁን የሰው አገር ባዕዳ ዐይን እየማረከ የሚጋብዝ እንግዳ ከጥንት ጀምሮ እንደ እሚታወቀው ጠላት የሚያፈራ ለምለሙ መሬት ነው። ለምለሙ መሬት ነው ጦርነት አብቅሎ ቤት አልቦ ያስቀረኝ ከቀዬ አፈናቅሎ። ለም መሆኑ ቀዬ አፈረ – መሬቱ ጠላቶቸን ጋብዞ ዛሬም እንደ […]

ለመለስ የተፃፈ ደብዳቤና የመለስ መልስ

$
0
0
ከፍቃዱ ጌታቸው ለመለስ እንደምን አለህ ጋሼ እንደምን ነህ መለስ ትመጣለህ ስንል ቀረህ ሳትመለስ እኛማ ይሔውልህ ባንተ ሌጋሲና ባንተ ትልቅ ራዕይ በየአደባባዩ እንላለን ዋይ ዋይ ዛሬም ጀነራልህ ተኩስ ነው ትዕዛዙ ወገን ያጋድማል የግፍ አፈሙዙ ለምንድን ነው ስንል ስምክን አስቀድመው ከክርስቶስ በላይ ምስልህን አትመው ቅዱስ መጽሐፍ ይመስል ባንተ ራዕይና በሌጋሲህ ምለው ቢረፈርፉንም አላለቅንምና ደብዳቤ ላክንልህ ከሞት የተረፍነው! […]

ላም እሳት ወለደች!

$
0
0
አጉል ዘመን ገጥሟት በረት ብትከሳ፤ ከብቶች በመዥገሮች አዩ ብዙ አበሳ፡፡ ጡቶቿን አቃጣይ የነበልባል ጥጃ ላም እሳት ወለደች፤ ብ’ተው በማይተዋ ዘልለው ባልጠገቡ ወይፈኖች ነደደች፡፡ የከበረው ባህል ባለጌ ረጋግጦት እንደጨው ቀለለ፤ ወፍ ዘራሾች ነግሠው ባጥለቀለቁት ደም ምድር ተበከለ፡፡ አዎ፣ ላም እሳት ወለደች! እንደዮዲት ጉዲት እቶኑ የሚፋጅ፤ ዕረፍት በማያ’ቅ ሠይፍ እንደነደርቡሾች እንደግራኝ አህመድ፤ ጭንቅላትን ገምሶ አንገትን ቆራርጦ ዜጎችን […]
Viewing all 162 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>