“ደሸት” የብርሃን እውነት! የማጂ፣ የጂማ፣ የመንዲ፣ የመደባይ አባት የማራ፣ የዥማ፣ የገንቲ፣ የአሬቲ … አያት የአማራው፣ የኦሮሞው፣ … የዘር ግንድ አውራ የመተሳሰሪያ እውነተኛ ምንጭ አሻራ! “ደሸት” ኢፋ ዹጋ ፍጥረተ ማለዳ የዘር ሀረግ ገመድ ምስጢራዊ ጓዳ አባ ቃሉ አባ ውሉ አያ ፍቅሩ ትስስሩ ዘረ ሸጋ ኢፋ ዹጋ መሆንህን አምኖ አማራ ኦሮሞ ስምህን በስሙ አትሞ “ደ”ን ደግ ብሎ […]
↧
“ደሸት” የብርሃን እውነት!
↧
ገድለህ ማረው
የሰራህን በዓይንህ አይተህ ሲወሻክት ወይም ሰምተህ ልታቆመው ብትነሳ በዝምታ ፊት ብትነሳ አፍሮ ይተው እንዳይመስልህ ስምህን ነው ሚከትፍልህ ከዛ – ይልቅ ነገርህን አ’ርገህ ድብቅ ትንሽ ጊዜ ብትጠብቅ እንደወትሮው ሱሱን ሊያደርስ ካ’ንዱሊቀምስ ካ’ንዱ ሊልስ ከሰው ጋራ ሲቀላቀል ባልታሰበ የፊት ተንኮል ተይዞልህ ፊትህ ሲቀል መፋረጃህ ያን ጊዜ ነው ተቀላቅለህ አብረህ በለው ወይንም በዓይንህ ገድለህ ማረው (ወለላዬ ከስዊድን)
↧
↧
በትዕቢት አይሆንም….
ባልና ሚስት ሆነን መስርተን ትዳር ልጆችም አፍርተን አንዳችም ሳይቀር ተመሥገን ፈጣሪ ምኞቴ ተሟላ አልቀይርም ሕይወት ይሄንን በሌላ ተሥፋ ለወደፊት ምሥጋና ሣሰማ ነገሩ ሌላ ነው ለካሥ ያንቺ ዓላማ የወለድናቸውን ልጆች በየተራ መንፈሥ እየቀየርሽ በተንኮል በሤራ እየመከርሻቸው የመለየት ሥራ ቤታችን ነገሠ ኩርፊያ አተካራ የገነባነውን ሐብትና ትዳር መጠበቅ ሲገባን በጋራ በምክር አንቺ ትብሽ እኔ በለን እንደአዋቂ ቀጣይ ትዳር […]
↧
ኢትዮጵያዊ ነኝ!!
አርነት ! _ የጥቁር ምድር አርማ ፤ ልዕልና ! _ የጥቁር ክብር ማማ፤ የጥቁር ደም – የጥቁር ዘር፤ የጥቁር ብቃይ – ከጥቁር አፈር፤ አንደበት !_ የፍሰሃ ቃል፤ ፋና ወጊ !_ የጥቁር ቀንዲል፤ አብሳሪ !_ የጥቁርን ልዕልና – የጥቁርን ድል ፤ ምንጭ ! _ የሰው ልጅ ዘር ግኝት፤ ማህተም ! _ የጥቁር ሕዝብ ዕሴት፤ ማተብ ! […]
↧
“ዕድሜ ለግንቦት ሃያ…”
በግንቦት 20 ዋዜማ ዋልታ ቴሌቪዥንን እያየሁ ነው። ጋዜጠኛው ዝግጅቱን ከአመት አመት በማይቀየሩት መፈክሮች (ለምሳሌ “ግንቦት 20 የህዝቦች ሁሉ የዘመናት ጥያቄ ምላሽ ያገኘበት ቀን ነው) ጀመረና፣ ዛሬም በጭንቅላቴ ውስጥ የሚፈነጩትን ጥያቄዎች ዘርዝሬ ለማሰብ እንኳን እድል ሳይሰጠኝ፣ “ከግንቦት 20 ወዲህ የተወለዱ ልጆች ስለዚህ ቀን ምን ያውቃሉ?” ብሎ ለመጠየቅ በየትምህርት ቤቱ መዞር ጀመረ። የ17 አመቷ ቆንጅዬ ልጅ በፍፁም […]
↧
↧
አውቀን እንታረም
ደራሲ፤ አቢይ አበበ (ሌ/ጄኔራል) ቅኝት፤ መስፍን ማሞ ተሰማ ዓለም ገና ልጅ ናት አውራጃዋም ደግሞ አርጅቶ የሚሞተው ሰው ብቻ ነው ቀድሞ ብዙ አሳልፋለች ብዙዎች ተክታ የሁሉንም ምግባር በየተራው አይታ። ሌ/ጄ አቢይ አበበ እንዲህ ሆነ፤ ርዕሱን አነበብኩና ደራሲውን ስመለከት ሌተናንት ጄኔራል ይላል። የህትመት ዘመኑ ደግሞ 1955 ዓ/ም። ባለሁበት ዘመን ውስጥ ሆኜ ሳሰላው እንግዲህ መፅሀፉ ከታተመ ግማሽ ምዕተ […]
↧
አስናቀ እንግዳ ይድረስህ ምስጋና
አስናቀ እንግዳ ገና ከጠዋቱ፡ ጎህ እንደቀደደ፡ ገና በማለዳ ከቆላ ከደጋ ተሸክሞ ዕዳ ከደቡብ ከሰሜን ከምዕራብ ከምሥራቅ ዘልቆ በመደዳ ለሀገሩ ለቀዬው ሰው እንዳይሆን ባዳ አበው ያወረሱት ታሪክ እንዳይጠፋ መላውን ዕድሜውን ያለ ቀና ደፋ ሀሰትን ኮንኖ፡ ሀቅን ይሚያፋፋ ምዝበራን ተጋፍጦ፡ ለሕዝብ የተዋጋ አልገዛም ያለ ላምባገነን መንጋ ሕይወቱን አስተምሮ፡ ሕይወትን የኖረ ንዋይ፡ ሀብት፡ ዝና ከቶ ያላፈቀረ የዕድሜ ባለጸጋው […]
↧
“ተዋከበና!”
ለቴዲ አፍሮ ዉበት ያምራል እንዴ? ቁንጅናስ ያምራል? አንዳንድ ጊዜ ሰዎች “I didn’t do nothing” ወይም “I didn’t say nothing” ሲሉ መስማት አዲስ አይደለም። እጅግ በጣም አልፎ አልፎ ቢሆንም፣ እንግሊዝኛ ያፍ መፍቻ ቋንቋቸው የሆኑ ሰዎችም ሲሉት ይሰማሉ። በቋንቋው ህግ መሰረት ይህ አ/ነገር ጎደሎ ነው። “double negative” የሚፈጥረው የ“positive” ትርጉም/ፍቺ ግድፈት ይመስለኛል። ሁለት ነጌቲቭ (“didn’t” እና “nothing”) […]
↧
…ቅምሻ…
በቀረችው ትንፋሽ … አገሩን አስታሞ … እሱም እንደ ሌሎች … ሊያሸልብ ነው ደግሞ! …………………………………………………. እንደ ሸረሪት ድር … ነገር ተወሳስቦ… እውነትን ማን ያውጣት … ከመሃከል ስቦ…? ………………………………………………… አገር ተሰቃየች…ጣሯ ብቻ በዛ.. ግማሹ እየሸጣት…ግማሹ እየገዛ…! ………………………………………………… የሰው ዘር መገኛ … ብለው ሲጎበኙን… በብሄር ተጠምደን … ተከፋፍለን አዩን:: ………………………………………………… ማን እንደዘረፈኝ … ልቤ እያስተዋለ የለመደው አፌ … […]
↧
↧
“ደግ ሰዉ አለፈ ..”
አባት ያቆየዉን ልጅ እዲጠብቀዉ የተከበሩ ኮ/ል አስናቀ እንግዳ፤ ኢትዮጵያን ለሚረከበዉ ወጣት ትዉልድ አዘዉትረዉ እንዲህ ይሉ ነበር። “አንተ የዛሬ ትዉልድ ሆይ! አንድ ጊዜ ቆም ብለህ አዳምጠኝ። ከተቻለ አባቶችህ ከሠሩት ላቅ ያለ፤ በስተቀር የእነሱን ያህል ካልሠራህ ሐገር አይኖርህም። የእኔ ትዉልድ በስልጣኔ ኋላ ቀር ቢሆንም፤አባቶቹ ከሠሩት በላይ አከናዉኖ አደራዉን ተወጥቶ፤ሀገሪቱን አስረክቦሃል።አንተም ለልጆችህ ይህችን ጥንታዊ ሐገር በክብር ለማስረከብ እንድትችል፤ […]
↧
ካየሁት ከማስታውሰው
ማስታወሻ ከቃኚው፤ ይህ የልዑል ራስ እምሩ ሃይለ ሥላሴ መፅሀፍ ቅኝት በቅድሚያ ጥቅምት 2004 ዓ/ም – ኖቬምበር 2011- በሌሎች ድረገፆች ላይ ለንባብ ቀርቧል። በዚህ ወቅት በጎልጉል ድረገፅ ጋዜጣ ላይ መቅረብ ያስፈለገበት ምክንያትም በቅርቡ ጎልጉል ‘የኢትዮጵያ አርበኞች ውለታና የባንዳዎች ዕዳ’ በሚል በግንቦት ወር ላይ አርበኞቻችንን ለመዘከር ባወጣው ፅሁፍ ራስ እምሩ ከ’ባንዳዎች’ የስም ዝርዝር ውስጥ መካተታቸው ባስነሳው ውዝግብ […]
↧
New book unveils 12 soft skills that make or break one’s success
FOR IMMEDIATE RELEASE Press Release Soft Skills That Make or Break Your Success: 12 soft skills to master self, get along with, and lead others successfully by Assegid Habtewold- a leadership expert and soft skills workshop facilitator, is now available. The book is based on a story and shares great insights, approaches, and […]
↧
ስምህን ሳላነሳ፣ የተወጋ አይረሳ!
ስምህን ሳላነሳ፣ ምኑን ሆንከው ፀጋ ለአብሮነት መኖር፣ እየሆንክ አደጋ፣ አድርገህ ከያዝከው፣ የሙሉቀን ሥራ ለማቃባት ደም፣ ኦሮሞን ካማራ። ‘ጀሃዳዊ ሃረካት’፣ እና ‘አኬል ዳማ’ በለምለሟ አርሲ፣ በአኖሊ ከተማ ወያኔ ያቆመው፣ የጥላቻ ሃውልት የተሸከመው እጅ፣ የተቆረጠ ጡት ሆነ ውጤት አልባ፣ አነሰ አሉህ እንዴ አሽከርካሪዎችህ፣ ፍጠር ሌላ ዘዴ? ጦርና ጎራዴ ሕዝቡን ለማማዘዝ ድንገት ቱግ ብለህ፣ የምትረጨው መርዝ። ዕውቀት ነበርኮ፣ […]
↧
↧
ትዝታ –ሀዲስ አለማየሁ
ቅኝት – መስፍን ማሞ ተሰማ የቃኚው ማስታወሻ፤ ጎልጉል ድረገፅ ጋዜጣ ጁላይ 2 / 2017 “ራስ እምሩን በተመለከተ” በሚል ርዕስ አንድ ፅህፍ ለንባብ አብቅቷል። ይህ የጎልጉል ድረገፅ ጋዜጣን አቋም ያንፀባረቀው ፅሁፍ ሙያዊ ሥነምግባርን (ፕሮፌሽናል ኤቲክስ) ከብቃትና ከሃላፊነት ጋር ያዋደደ ስህተቱንም በግልፅና ያለማወላወል የተቀበለና ለእርማቱም መፍትሄን ያመላከተ መሆኑ የድረገፁን ዝግጅት ክፍል የሚያስወድሰውና በአርአያነትም ከመጀመሪያው ረድፍ የሚያቆመው ይሆናል። […]
↧
ትልቅ ሰው ትልቅን
ይባላል … ድሮም ይነገራል ትልቅ ሰው ትልቅን ያስከትላል ሲባል በፊትም ሰምተናል ይኸው ዕውነት ሆኖ ሲፈጸም አየን ቃሉ በነጋሽ ገ/ማርያም፣ በተስፋዬ ሳህሉ የሐምሌ ወርን የሰላሳ ቀናት እቅፍ በነኀሴ ተክተን ሳናልፍ ሁለቱን ታላላቅ የጥበብ ከዋክብት አከታትለን አጣን የአዛውንቶች ክበብን ዘጋን ፀጋዬ ገ/መድህን በጻፈው አባተ መኩሪያ ባዘጋጀው አውላቸው ደጀኔ፣ ወጋየሁ ንጋቱ በተጫወቱበት ዓለሙና ሲራክ አብረው በሆኑበት እነ አስናቀች […]
↧
ፎቶግራፍ እና አጼ ምኒልክ
ከውጪ ሀገር የመጡ ሰዎች ለአፄ ምኒልክ ስለ ፎቶግራፍ እንዲህ ብለው አስረዷቸው “በአውሮጳ አንድ ትንሽ ሳጥን አለች ሰውን፣ ፈረሱን፣ ቤተመንግስቱን ሁሉ ወደ ሳጥኗ ታስገባና ሁሉን ትንሽ አርጋ ታሳያለች” አሏቸው። ምኒልክም በሰሙት ነገር ተገርመው እንዴት ይሆናል ይሄን ነገር ማየት አለብኝ ብለው የፎቶ ማንሻ እንዲመጣ አዘዙ። የፎቶ ማንሻውም (ካሜራ) ከእነ አንሺው በ1875 ዓም ወደ ሀገራችን ገባ። ሆኖም ግን […]
↧
አታስብ ይሉኛል!
ማሰብ ማሰላል – ማጤን ማውጣት ማውረድ፤ ባ’ይምሮ መፀነስ – ሃሳብን ማዋለድድ፤ ከምናብ ጓዳ ውስጥ – ምስጢርን ፈልፍሎ፤ ያይምሮ መረዋን – ማንኳኳት ደውል :: መላ ማፈላለግ – እንዲህ ቢሆን? ማለት ፤ አይምሮን ኮትኩቶ – ዕውቀት ዘርቶ ማምረት፤ ባ’ንዱ ውስጥ ሌላው_ በሌላው ውስጥ አንዱ_ እንዳለ መረዳት:: (ሙሉውን ግጥም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) አሥራደው (ከፈረንሳይ)
↧
↧
ጣምራ ቁስል
ደራሲ፤ ተስፋዬ መኮንን ባይለየኝ (ዶ/ር) ቅኝት፤ መስፍን ማሞ ተሰማ ቀዳሚ፤ እነሆ ከጣምራ ቁስል በፊት “ቀይ አንበሳ” ነበረ። እነሆም ስለ ‘ቀይ አንበሳ’ ‘በማንኪያ’ እናቀምሳለን። እንዲህ ብለን፤ አልኻንድሮ ዴል ባዬ ኩባዊ ነው። ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት ለንደን፤ እንግሊዝ ውስጥ ነበር። በወቅቱ በእንግሊዝ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት ሀኪም ወርቅነህ ማርቲን (ደብሊው ማርቲን) በጋዜጣ ላይ ባወጡት ማስታወቂያ አነሳሽነት አምባሳደሩ ፊት […]
↧
ሞት የሰጠን ደስታ
የታጨደው ሳር ድርቆሽ ነው የከብቶች መኖ በመሆን በበሬ ጫንቃ ድካም ጠግቦ አደር ያደረገን፤ የሞተው የግጦሽ ሳር ነው ጮሌ ፈረስ አሳድጎ በጦር ሜዳ የድል ብሥራት ያቀዳጀን ጀግና ተዋጊ አድርጎ፤ የበሬውን ቆዳ ከበሮ የበሬውን አንጀት ጅማት የፈረሱን ሞት በደል የሸንበቆውን ያካል ስብራት፤ የእንስሳቱን ሞት ከእሳሩ ሞት ጋር ስናዋድደው ከሞት […]
↧
ሐተታና ግምገማ፤ የማለዳ ድባብ [የአዳዲስ ግጥሞች መድብል]
የማለዳ ድባብ [የአዳዲስ ግጥሞች መድብል]፤ 2009ዓ.ም፤ አ/አ፤ አታሚ አልተገለጸም፤ 10ዶላር፣ 100 ገጽ የማለዳ ድባብ፣ ለ በዕውቀቱ ሥዩም አራተኛ የግጥም ሥራው ነው። መጽሐፉ ሦስት ክፍሎች አሉት፤ “ግጥምና የዘመን መንፈስ” [ገጽ 5-9]። ግጥሞች [ገጽ 17-91]። “ጉደኛ ስንኞች” እና “ሙሾና ባለቅኔ” [ገጽ 93-100]። መድብሉ፣ ቀድሞ ካስነበባቸው ላይ አዳዲሶች ተጨምረውበት የተዘጋጀ ነው [ገጽ 9]። የትኞቹ አዳዲሶች እንደሆኑ አልተገለጸም። ግጥም […]
↧