Quantcast
Channel: Goolgule
Viewing all 162 articles
Browse latest View live

ደንቁሩ በአዋጅ!

$
0
0
እግዚአብሔር ዓይንን ፈጠረና እዩበት አለ፤ እግዚአብሔር ጆሮን ፈጠረና ስሙበት አለ፤ እግዚአብሔር አእምሮን ፈጠረና አስቡበት አለ፤ እግዚአብሔር አንደበትን ፈጠረና ተናገሩበት አለ፤ ወያኔ አይሆንም አለ! በዓይንህ አትይ፤ በጆሮህ አትስማ፤ በአእምሮህ አታስብ፤ በአንደበትህ አትናገር፤ አበሻ ተዋረደ! ዓለም እየሰማ ድንቁርና ታወጀበት! ማን ያሸንፋል? እግዚአብሔር አለ፤ ወይስ ወያኔ አለ? (ምንጭ: Prof. Mesfin Wolde-Mariam Blog)

“ምጽአተ ዐማራ”አዲስ መጽሐፍ

$
0
0
ይህ መጽሐፍ ባለ 657 ገፆች ነው። በዘጠኝ ምዕራፎች ተከፋፍሏል። እነርሱም፦ የኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት መከፋፈል፣ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ኃይማኖት ተከታዩና ዐማራው የከፈሉት ዋጋ የኢትዮጵያ አንድነት ትንሣኤ፣ የዐማራው የአንድነትና የፀረ-አንድነት ትግል ውጤት ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ፤ የፍፁማዊ ዘውዳዊ አገዛዝ የአንድነት ግንባታ ሂደት ድምድም እና የኢትዮጵያ ዳግም ብተና ጽንስ የለውጥ ፈላጊው ትውልድ የኃይል አሰላለፍ ዘረኛው የትግሬ-ወያኔ ከ1972 እስከ 2007 ዓም ድረስ በዐማራው […]

“…የጦር ኃይል …እና የብእር ኃይል …”ሃዲስ አለማየሁ

$
0
0
” … ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ አሁን እስካለንበት ድረስ ታሪኩን መለስ ብለን ብንመለከት በሰው ዘር ላይ ግዛታቸውን ለመዘርጋት፣ ሰውን ባካልም ሆነ በመንፈስ ለመግዛት፣ ሁለት ተቃራኒ ኃይሎች ሲታገሉ እናያለን፡፡ ከነዚህ አንዱ የሀይለኞች፣ ያጥቂዎች፣ የጦር ኃይል፣ ሁለተኛው የደራሲያን የብእር ኃይል ናቸው፡፡ “የጦር ኃይል በየጊዜው፣ በየቦታው የሚነሱ ኃይለኞች ሰራዊት አደራጅተው፣ የጦር መሳሪያ አከማችተው፣ ሰውን እየጨቆኑ ለግል ድሎታቸውና ፍላጎታቸው አገልጋይ […]

“ትራምፕ –ቢመረጥስ?! …”

$
0
0
… በበረዶ፣ በዝናም፣ በሐሩር፣ በቁሩ . . . መፈክር አንግበን፣ ላንቃችን እስኪታይ – አምባገነኖችን በጩኸት አውግዘን፣ የድምጽ-አልባውን ሕዝብ – የጭቆና ብሶት፣ ላለም ስናሰማ – ለሩብ ምዕተ-ዓመት፤ ጆሮ ዳባ ብለው – የተሳለቁብን፣ ከጨቋኝ ወግነው፣ በዶላር አፋፍተው… ነጻነታችንን በጅ-አዙር ያስቀሙን. . .፤ ቦ! ጊዜ ለኩሉ!… የተፈጥሮ አዙሪት-ህግ – የወር-ተራው እዚያም ደርሶ፣ በታላቋ አሜሪካ – “አምባገነን” ትራምፕ ነግሶ፣ […]

ይረገም!!

$
0
0
በክፉ ያነሳ ወርቃማውን ስምሽን፣ በሃሜት ያጎደፈ ፀዐዳ ክብርሽን፣ በክፋት ፈረሱ ወዳንቺ የጋለበ፣ በእሾኸም ምላሱ ሊወጋሽ ያሰበ፤ ሰላምሽን የነሳ፣ ባንቺ ላይ ሊሳለቅ፣ ሊቀልድ የቃጣ መልካም ህይወት ትክዳው! ነፍሱ ሰላም ትጣ!! ብርሃንሽን ሊያጠፋ ውበትሽን ሊያከስም፣ መዐዛሽን ሊበክል ህይወትሽን ሊያጨልም፣ በክፋት ያቀደ በሻገተ ህሊናው፣ ብርሃኑ ይደፈን ! ጨለማ ይውረሰው! ስትለመልሚ ስትፈኪ አይቶ፣ በአርኪ ፈገግታሽ በቅናት ተውጦ፣ የቆሸሸ እጁን […]

ያለም ገዥ

$
0
0
ኮሳሳ አገዝፎ፣ ግዙፍ አኮስሶ የሾመውን ሽሮ፣ያሻውን አንግሶ በለወጠው አዲስ ክስተተ ሁኔታ ሀዘንና ደስታ፤ ደስታና ሀዘንን አቀያይሮ ቦታ በራሱ ህግጋት ዘመኑን ዳኝቶ ጊዜ ነው የሚኖር ዓለማችን ገዝቶ። ጥቅምት 2009 አብርሃም በየነ

የግርማ ይፍራሸዋ ፒያኖ ኮንሰርት በዋሺንግተን ዲሲ

$
0
0
ከ25 ዓመታት በላይ የፒያኖ ድርሰቶችን በመጻፍና በመጫወት የአገራችንን ስም በማስጠራት የቆየው ኢትዮጵያዊው ዜማ ደራሲ እና ፒያኒስት ግርማ ይፍራሸዋ በአሁኑ ቅዳሜ November 26 ምሽት ከ6:30 ጀምሮ በዋሺንግተን ዲሲ እና በአካባቢዋ ለሚገኙት አድናቂዎቹ ግሩም የሆነ የፒያኖ ሙዚቃ ትርኢት Washington Ethical Society አዳራሽ ለማቅረብ ተዘጋጅቷል። ግርማ የሙዚቃ ትምህርቱን የጀመረው በልጅነቱ ክራር በመጫወት ነበር። በመቀጠልም በያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት (1975-1978 […]

ለጀግናው አትሌት ስንብት!

$
0
0
. . . በዚያ ቀውጢ ጊዜ – በዚያ ቀውጢ ዘመን፣ ከአገር በራቀበት – የደስታ ሰመመን፤ ያገር ፍቅር ስሜት –  መገለጫ ፈርጦች፣ ብቸኛው አማራጭ – የደስታችን ምንጮች፣ ነበሩን! ነበሩ! “አረንጓዴ ጎርፎች”. . .፤ እንዲህ እንደዛሬው – ሳይዘምን ዘመኑ፣ ያለም መገናኛ – ሳይራቀቅ ኪኑ፣ ዩ ቲዩብ፣ ኢንተርኔት፣ ስማርት ፎን..ሳይኖር፣ ዜና መቀበያው – ራድዮናችን ነበር፤ “. . . […]

የዛ ሰውዬ ድምጽ . . .

$
0
0
ፊቱ አሸቦ መስሎ፣ እንደደነገጠ፣ ተጎልጉሎ ወጥቶ፣ ዓይኑ እንደፈጠጠ፣ ባንኮኒው ጋ ሄዶ፣ ቢራውን ጨበጠ። የሆነውን እንጃ! ሁኔታው ያስፈራል፣ እንባው በጉንጩ ላይ፣ አቋርጦ ይፈሳል አልቅሶ ሲበቃው፣ ውጪ እየሰለለ፤ ያየውን በውስጡ፣ እያሰላሰለ፣ ገድለው ሲጥሏቸው፣ በዓይኖቼ አየሁ አለ። ወደ ተናጋሪው፣ አፍጠን እያየን፤ እንደልማዳችን፣ ዝም ተባባልን። ሰውዬው ቀጠለ፣ ገድለው ሲጥሏቸው፣ በዓይኖቼ አየሁ አለ! ዘለው ያልጠገቡ፣ እህል የተራቡ፣ አገር የተቀሙ፣ ፍትሕ […]

“[ሰዎች] አለሙያቸው ሙያ እየጫንባቸው አበላሽተናቸዋል”ወለላዬ

$
0
0
ሰላም ጎልጉሎች . . . እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ። ከኢትዮጵያ ዛሬ ጋር በግጥሞቼ ሳቢያ ቃለ መጠይቅ አድርጌ ነበር። እናንተም ግጥሞቼን በተገቢው ሁኔታ ያስተናገዳችሁልኝ ስለሆነ እናንተም (ዘንድ) ቢታተም እወዳለሁ። በድጋሚ መልካም በዓል ይሁንላችሁ። ወለላዬ መዝጊያ ትሁንልኝ መቶ ራት ግጥሞችን – ተሸክሜ ይዤ፤ ረብዕ ረቡዕ ስጥል – አንድ አንዷን መዝዤ በዚች ባሁኗ ቀን – በጨበጥናት ሳምንት፤ […]

የተካደ ትውልድ

$
0
0
የተካደ ትውልድ አይዞህ ባይ የሌለው ታዳጊ የሌለው ወይ ጠባቂ መላክ፤ ወይ አበጀ በለው ደርሶ ከቀንበሩ የማይገላግለው የተካደ ትውልድ፤ አብዝቶ የጾመ፤ ተግቶ የጸለየ ጥቂት  መና ሳይሆን፤ ጥይት ሲዘንብ ያየ እድሜ ይፍታህ ተብሎ፤ የተወለደ’ለት አምባሩ ካቴና፤ ማተቡ ሠንሠለት፡፡ ምቾትን የማያውቅ፤ ረፍት የተቀማ አልጋው ያጋም እሾህ፤ ምኝታው የሣማ የተካደ ትውልድ፤ ሞቶ እንኳ ሬሳው፤ አይላላለት ቀንበር በዘብ  እጅ ተገድሎ፤ […]

“እኩል ደራ ደራ ከነ‘ሜቴ ጋራ!”

$
0
0
ገጣሚና ደራሲ… ከግዑዙ መሬት፣ ከመንደሩ ይልቅ ከዘር ማንዘሩ፣ ሰብዓዊነትን ያልማል ብዕሩ “የሰው ልጅ ልብ…” ነው አገሩና ድንበሩ! ሰብዓዊነት ነው ክብሩ፤ ገጣሚ አገር የለውም፣ “ዩኒቨርሱ”ም አይበቃውም፤ ሰዋዊ ህመም ያመዋል፣ ፈውሱም ይፈውሰዋል፣ ገጣሚ ያ ይበቃዋል! ወርዶ ወርዶ “ቀየ መንደር ውስጥ አይወድቅም” አዎ! ገጣሚ፣ ደራሲ እንዲያውም አገር የለውም፣ የበዓሉ አገሩ ሰው ነው፣ “…ህንጻው ምን ቢረዝም፣ ምን ቢጸዳ ቤቱ፣ […]

“የተቆለፈበት ቁልፍ”በቃላት ቁልፍ ተቆላልፏል!

$
0
0
ለረጅም አመታተ የጣልኩትን ብዕር ድር ካደራበት ሰገባው እንድመዝ አስገደደኝ – በ ኢትዮ-ሚዲያ (Ethiomedia) እና በጎልጉል (Googlgule) ድህረ-ገፆች ላይ ከወራት በፊት በዶክተር ፍቃዱ በቀለ በተባሉ ግለሰብ በ”የተቆለፈበት ቁልፍ” መፅሐፉ ላይ የቀረበ አንድ ፅሑፍ። “ሃያሲው” በዘመናችን አቻ ያላገኙለት (ወደር የሌለው) መፅሐፉ መሆኑን ነው የገለፁልን። “…የስነ-ጽሁፍም ዋና ዓላማው በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ ያሉትን አስቀያሚም ሆነ ቆንጆ ነገሮች ስዕላዊ በሆነ […]

ላንዲት መስቲካ ሻጭ ህጻን

$
0
0
በደብተርሽ ምትክ ትንሽ ሱቅ ታቅፈሽ ካልፎሂያጅ እግር ስር፤ እንደ ድንቢጥ ከንፈሽ ጋሼ ግዙኝ ስትይ፤ ኣንጋጠሽ ወደ ላይ ለጉድ ተጎልቸ፤ ምታረጊውን ሳይ ራሴስ ይታመም፤ ምላሴን ምን ነካው ግራዋ ይመስል፤ መረረኝ ማስቲካው:: ኣፈር ጠጠር ለብሶ ፤በዶዘር ተድጦ መስኩ ከነጎርፉ ሰማይ ከነዶፉ ለጌቶች ተሽጦ ኣተር ነው እያሉ፤ ኣፈር ዘግኖ መፍጨት ገነት ነው እያሉ፤ መስክ ላይ መፈንጨት ጠበል ነው […]

“አንተስ…?”

$
0
0
ዓይኔን በዓይኔ ያየሁበት፣ በስተእርጅና ያገኘሁት፣ የትናንቱ ማሙዬ፣ ያሳደኩት አዝዬ የንግሊዞችንወረራ ሰምቶ፣ በቴዎድሮስ ሞት ተቆጥቶ፣ ለምን? ለምን ሞተ? ብሎ ሲያለቅስ፣ የዓይኑን ዕንባ ላደርቅ- የልቡን መሰበር ላድስ፣ ጀግኖቻችንን ቆጥሬ- ታሪካችንን ባወድስ፣ ዕንባውን ዋጥ አድርጎ- በአትኩሮት ዓይኔን እያየኝ፣ «አንተስ…?» አንተስ!- ምን ሰርተሀል? በማለት ጠየቀኝ። እድሜ ቢደራረብ ተግባር ሳይላበስ፣ እንደዚህ እንደኔ ያስጠይቃል ለካስ! (ወለላዬ)

አዲስ እንደ ቬኒስ

ዕዘኑ ለቀሪ

$
0
0
የመቅደላው ደባ ቋጠሮ የተቀበረው በቂም ጓሮ የምስጢሩ ገመና ለሥልጣኑ ንግሥና ከጠላት ጋር ወግኖ በተቸረው ኃይል መቅኖ መይሳውን አስገድሎ ለመግዛት ተደላድሎ በትረ መንግሥቱን ምራጭ ካሳ የጨበጠበት ድርጊት ጠባሳ ደረስጌን በውቤ ብሎ የቂም ብድሩን ከፍሎ የጎንደሮች መሬት ቁርሾ የበደሉ ዋይታ ሙሾ የግፉ ክፋት ገመና ይደረደራል ገና በበገና በበገና። ያችን የሙታን እናት አጉል ድከሚ ብሏት ያለ ፋይዳ ከንቱ […]

ደም ነው ሥርየቱ

$
0
0
ዐባይ ቢሻው ይጉረፍ በጣና ላይ ነግሶ አሎሃ ይደፍርስ ተከዜም ደም ለብሶ ማሂንም አቋሽም ጓንግም በሙላቱ መሻገሪያ ይንሳ እስኪያልፍ ክረምቱ ይፎክር ያቅራራ ይኩራ በጉልበቱ ድሮም እንዳይፀዳ በጎርፍ ውኃ ታጥቦ የጀግና ሰው ሞቱ ያውቃሉ እናውቃለን ዛሬም እንደ ጥንቱ ደም በደም ይፀዳል ደም ነው ሥርየቱ። ለጀግና ዕምባ አይረጩም ፀጉርም አይላጩም ዋይታና ለቅሶ ሙሾ አይደረድሩም ወይም ፊት አይነጩም እንደ […]

Kidane Alemayehu, My Journey with the United Nations and Quest for the Horn of Africa’s Unity and Justice for Ethiopia

$
0
0
The journey which author Ato Kidane Alemayehu chronicles in his new book takes him through Lesotho, Tanzania, Uganda, United Arab Emirates and the Horn of Africa as a representative of the United Nations, and ultimately to establish an organization dedicated to confronting “Fascist Italy and the Vatican.” His book contributes valuable information to the history […]

ወንዙ እና ዛፉ

$
0
0
ስርሽን አየሁት ቁልቁል ተዘርግቶ፣ ረዝሞ ተባዝቶ፣ አንድ አንቺን ሊያሳድግ፣ አንድ አንቺን ሊያቀና፣ እጅግ ተበራክቶ፣ በዚህ ከቀጠለ የጉዞ ርዝመቱ፣ ውፍረት ከጨመረ፣ ካደገ ቁመቱ፣ ወንዙ አንጀቱ ታልቦ፣ መቅኒው ተመጥምጦ፣ አፅመ ወዙ ደርቆ፣ ደም ውሃው ተመጦ፣ መላ አካሉ ፈርሶ እርቃኑን ተጋልጦ፣ ባዶ መቅረቱ ነው ድንጋይ ጥርሱ ገጦ፣ ወለላዬ ከስዊድን (welelaye2@yahoo.com)
Viewing all 162 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>